Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 6ኛው የኢትዮጲያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ምስለ ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆነ

6ኛው የኢትዮጲያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ምስለ ችሎት ውድድር ከሚያዚያ 27-30/2014 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና በኢ.ፌ.ደ.ሪ ፍትህና ሕግ ኢኒስቲውት የጋራ አዘጋጅነት በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተካሔደ ሲሆን የድሬደዋ ዩኒቨርሲት ሕግ ኮሌጅ በዛሬው ለት የተካሄደው የፍፃሜ ውድድር መድረስ የቻለ ሲሆን በአምስት ዳኞች በተሰጠው ድምር ውጤት የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል።

ውድድሩ ለሁሉም የኢትዮጲያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ክፍት የሆነ ሲሆን የቃል ክርክሩ ላይ የሚሳተፉ ዩኒቨርሲቲዋች በውድድሩ የፅሁፍ ዙር ባስመዘገቡት ውጤት የተመረጡ ናቸው። የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ኮሌጅም የውድድሩ አሸናፊ ከመሆኑ በተጨማሪ ለውድድሩ ከተዘጋጁ አምስት ዋንጫዋች አራቱን መውሰድ ችሎአል። ውድድሩ ለይ የተሳተፉ ተማሪዋች:

1. ተማሪ አይዳ ብርሀኔ

2. ተማሪ ሀይማኖት ኤፍሬም

3.  ተማሪ ሳውዳ ጀማል ሲሆኑ መምህር አብይ ደምሴ የተማሪዋቹ አሰልጣኝ በመሆን ተሳትፎአል። 

በውድድሩም ተማሪ አይዳ ብርሀኔ የውድድሩ ፍፃሜ ዙር ምርጥ ተናጋሪ ስትሆን ሀይማኖት ኤፍሬም የውድድሩ ምርጥ ተናጋሪ እንዲሁም ምርጥ ሴት ተናጋሪ በመሆን ውድድሩን ጨርሰዋል። 

ከዚህም በተጨማሪ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ኮሌጅ አንድ መምህር በዳኝነት  አንዲሁም አንድ መምህር  በአዘጋጅ ኮሚቴ አባልነት በውድድሩ ላይ አሳትፎአል።

በሌላ በኩል የውድድሩ የፅሁፍ ዙር በተደረገው ውድድር ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የውድድሩ ምርጥ ፅሁፍ (best memorial) አሸናፊ ሆነዋል።

Share This News

Comment