Logo
News Photo

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 6ኛው ዙር ሀገር አቀፉ የህግ ትምህርት ቤቶች የምስለ ችሎት(ፍርድ ቤት) ውድድር አሸናፊ በመሆን የ4 ዋንጫ ተሸላሚ ለሆኑት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ኮሌጅ ተማሪዎችና መምህራን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

የምስለ ችሎት ( የምስለ ፍርድቤት) ውድድር በሀገራችን በሚገኙት  ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል የሚካሄድ ውድድር ሲሆን የዘንድሮውን የ6ኛው ዙር የምስለ ፍርድቤት ውድድር የደቡብ ክልሉ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ነበር ያዘጋጀው፡፡

ውድድሩ ለሁሉም የኢትዮጲያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ክፍት የሆነ ሲሆን የቃል ክርክሩ ላይ የሚሳተፉ ዩኒቨርሲቲዎች በጽሑፍ  ውድድሩ ላይ  ባስመዘገቡት ውጤት  መሠረት የተመረጡ ናቸው። 

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ኮሌጅም በግልና በቡድን በተደረገው ውድድር አሸናፊ መሆን የቻለ ሲሆን ለውድድሩ ከተዘጋጁት አምስት ዋንጫዋች መካከል  አራቱን መውሰድ ችሏል። 

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲን በመወከል በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ተማሪዎች ተማሪ አይዳ ብርሀኔ ፣ ተማሪ ሀይማኖት ኤፍሬም እና ተማሪ ሳውዳ ጀማል ሲሆኑ መምህር አብይ ደምሴ ደግሞ የተማሪዋቹ አሰልጣኝ በመሆን በውድድሩ ላይ ተሳትፏል። 

በውድድሩም ተማሪ አይዳ ብርሀኔ የውድድሩ ፍፃሜ ዙር ምርጥ ተናጋሪ ስትሆን ሀይማኖት ኤፍሬም የውድድሩ ምርጥ ተናጋሪ እንዲሁም ምርጥ ሴት ተናጋሪ በመሆን ሁለቱም ተማሪዎች ውድድሩን በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ ኮሌጅ አንድ መምህር በዳኝነት  አንዲሁም አንድ መምህር  በአዘጋጅ ኮሚቴ አባልነት ማሳተፍ ችሏል፡፡ 

በዚህ ውድድር ላይ አሸናፊ መሆን ለቻሉ የህግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ለተማሪዎቹ (የኮቺንግ) ስልጠና እና ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ መምህራን የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡

ለተማሪዎቹ በተደረገው የአቀባበል ስነ-ስረዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደምን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዘዳንቶች እና የተለያዩ የትምህርት ክፍል ሀላፊዊች ተገኝተው ለልኡኳን ቡድኑ የእንኳን ደስ ያላቹሁ መልእክት ያስተላልፉ ሲሆን በእንኳን ደስአላችሁ መልእክታቸውም ልኡካኑ ባመጡት ውጤት የዩኒቨርሲቲውን ስም ከፍ ብሎ መጠራት እንዲችል በማድረጋቸው ኮርተንባቹሀል ሲሉ አመራሮቹ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም ለልኡካን ቡድኑ በተዘጋጀ የእራት ግብዛ ላይ ይህ ውጤት እንዲመጣ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እና ውጤቱን ላመጡት ተማሪዎችና መምህራን የእውቅና የምስክር ወረቀት እንዲሁም የማበረታቻ ሽልማት በዩኒቨርሲቲው ተበርክቶላቸዋል፡፡ 

Share This News

Comment