Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባባያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በጋራ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመው  በቀድሞ መጠሪያው  የኢትዮጵያ ጨረር መከላከያ ባለስልጣን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ   የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ተብሎ ከሚጠራው ተቋም ጋር ነው፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በኩል የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የፈረሙ ሲሆን በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ባለስልጣን በኩል ደግሞ የባለስልጣኑ ጀነራል ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ጌታቸው ናቸው፡፡

በዚሁ ወቀወት ዶ/ር መገርሳ እንዳሉት በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገው የጋራ ስምምነት በቀጣይ በመማር ማስተማር ፣ በጥናትና ምርምር ለሚሰሩ ስራዎች አንድ ሀገርም ሆነ እደ አካባቢ ውጤታማ ስራዎችን ለመከወን የሚያስችል ነው፡፡

በተለይም የጨረርና የኑክሊየር ቴክኖሎጂ ለአንድ ሀገር እድግት ለከፋተኛ ሚናን የመጫወታቸውን ያህል የጎንዮሽ ጉዳት የሚያስከትሉ በመሆናቸው በዚህ ቴክኖሎጂውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የሆኑ አካልት በቂ ግንዛቤ ሊያገኙ ይገበል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ጀነራል ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ጌታቸው በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በጨረርና በኑክሊየር ቴክኖሎጂ ላይ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆንነ ገልጽው በተለይም በኃይል ማመንጫና በግበርናው ዘርፍ ይህንኑ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በማዋል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

የጨረርና ኑክሊየር ቴክኖሎጂ በማስፋት ሀገር የጀመረቸውን ፈጣን ልማት ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊጫወቱት የሚችሉት ሚና የላቀ ነው ያሉት ጀነራል ዳይሬክተሩ አቶ ጌታቸው ተቋማቸው በቀጣይነት ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራበትን ሁኔታ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በሁለቱ ተቋማት መካከል የጋራ የመግባቢያ ስምምነቱ ከመካሄዱ አስቀድሞ በመድረኩ ላይ ተሳታፊ ለሆኑ በዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ኮምፔቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና የላብራቶሪ ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡  

Share This News

Comment