Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በድሬዳዋ ለሚገኙ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ፡፡

የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ በድሬ ዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ ቁጥራቸው ከ25 ለሚበልጡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማሩ የሚያግዙ የተለያዩ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ 

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲው በአስተዳደሩ  የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ዘርፈ-ብዙ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑን ገልፀው በእለቱ የተደረገው ድጋፍም የዚሁ እንቅስቃሴ አካል መሆኑን ጠቁመዋል። 

በዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ወንዲፍራው ደጀኔ በበኩላቸው የትምህርት መርጃ መሳሪያዎቹ ድጋፍ የተደረገላቸው ቁጥራቸው ከ25 ለሚበልጡ የግልና የመንግስት 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሆኑን ገልፀው ድጋፉ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች የተመረጡትም ዩኒቨርሰቲው በ2014 ዓ.ም እየሰጠ  በሚገኘው የሳ.ቴ.ም.ሂ (STEM) ፕሮግራምና የሳይንስ ጥያቄና መልስ ውድድር (Science Olympiads) ላይ ተማሪዎቻቸውን እያሳተፉ ለሚገኙ ት/ቤቶች መሆኑን ተናግረዋል። 

እንደ ዶ/ር ወንዲፍራው ገለፃ እንዲህ አይነት ድጋፎች ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው  በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ከዩኒቨርሲቲው ጋር የበለጠ ተቀራርበው በመስራት ተማሪዎቻቸውንና መምህራኖቻቸውን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ሲሉ መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡ 

በመጨረሻም በእለቱ ድጋፉን የተረከቡ የየትምህርት ቤቶቹ ተወካዮች እንደተናገሩት ይህ የተደረገላቸው ድጋፍ ለትምህርት ቤታቸው ትልቅ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ገልፀው ለተደረጋላቸው ድጋፍ ዩኒቨርሲቲውን በማመሰገን ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ወደፊም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

Share This News

Comment