በዩኒቨርሲቲው ለዓመታት የዘለቀውን የንፁህ መጠጥ ውኃ ችግር ለመቅረፍ የሁለት ጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮና የመስመር ዝርጋታ ሥራ ተከናውኖ ከቅርብ ሳምንት በፊት ፕሮጀክቱ በይፋ መመረቁ ይታወሳል፡፡
ይህንኑ ተከትሎም ቀሪ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን በማጠናቀቅ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቱን አገልግሎት መስጠጥ እንዲጀምር ተደርጓል፡፡
የንፁህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቱ መጀመር ተከትሎ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተማሪዎች የመኝታ ክፍሎችና በተለያዩ አገልግልት መስጫዎች እየደረሰ ያለውን የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ አገልግልት መስጠት መጀመሩ ከዚህ ቀደም ከንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት እና ከመፀዳጃ ቤት ንፁህና ጋር ተያይዘው ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን ሙሉ ለሙሉ ከመቅረፍ ባሻገር ዩኒቨርሲቲው በቅጥር ጊቢው ውስጥ የጀመረውን ማስዋብ ስራ ከማሳካት አንፃር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል፡፡
የንፁህ መጠጥ ውኃ አገልግልት መጀመርን አስመልክተን ያነጋገርናቸው እንዳንድ ተማሪዎች እንደገለፁል ከሆነ ዩኒቨርሲቲው ከውኃ አቅርቦት ጋር ያለውን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት ችግሩ በተቻለ አቅም እንዲቀረፍ ያደረገበትን ሂደት አድንቀው በመኝታ ክፍሎቻቸው ውስጥ የሚገኙ በአንዳንድ የመፀዳጃና የገላ መታጠቢያ ቤቶችን የተጀመሩት የእድሳት ሥራዎች በተቀሩትም የመፀዳጃና የገላ መታጠቢያ ቤቶችተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ሃያ አምስት በሚሆኑ የተማሪዎች መኖርያ ህንፃ ላይ የመፀዳጃና የገላ መታጠቢያ እድሳት ለማከናወን የጨረታ ሂደት ላይ መሆኑን የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ተማም አወል ገልጸዋል።
Share This News