Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በክረምት የበጎፈቃድ ተግባራት በነበረው የላቀ ተሳትፎ የዋንጫና ሰርትፍኬት ተሸላሚ ሆነ፡፡

''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል መሪ ቃል የ2015 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች አስመልክቶ በተዘጋጀው የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ላይ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የነበረውን ተሳትፊ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በክረምት በጎፈቃድ መርሀግብሩ ደረጃቸውን የጠበቁ የ5 አቅመ ደካማ ነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶችን በማደስና በመገንባት ባበረከተው አስተዋፅኦ የዋንጫና የምስክር ወረቀት በሽልማት መልክ የተበረከተለት ሲሆን ሽልማቱንም ከእለቱ የክብር እንግዳ ከድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ፈቲሃ አደን እጅ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግልት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ተረክበዋል፡፡

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ድጋፍ ለሚሹ አካላት የመኖሪያ ቤት ግንባታና እድሳት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የግብርና ልማት፣ የማዕድ ማጋራት፣ የሙያ አገልግሎት፣ ትምህርት ለትውልድና የማህበረሰብ ጤና፣ የመሠረተ ልማት ማጠናከሪያ እንዲሁም የወጣት ስብዕና ግንባታ የመሳሰሉት ተግባራት በዋነኝንት የተከናወኑ መሆኑ በፕሮግራሙ ላይ ተገልፆል።

Share This News

Comment