Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የዲጂታል ክህሎት ስልጠና ተሰጠ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፣ ሻያ ሾኔ እና ከ50ዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በአገራችን በተመረጡ 50 ዩኒቨርሲቲዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የመማር ማስተማር ስርዓትን ( E-learning) ለመዘርጋት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው መሆኑ ይታወቃል።

የዲጂታል ትምህርት ስርዓትን eLearning ተግባራዊ ሊደረግባቸው ከታቀዱት 5 የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ሲሆን ይህንኑ የዲጂታል ትምህርትን በዩኒቨርሲቲው ለማስጀመር የሚያስችል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መደረግ ላይ እንደሆነ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ገልጸዎል፡፡

ዶ/ር ኡባህ አክለውም የዲጂታል የትምህርት አሰጣጥን ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው በቅርቡ የዲጂታል ትምህርቱን ለሚሰጡ መምህራን ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በዚሁ የዲጂታል ትምህርት አሰጣጥ ስርዓት ላይ ለተማሪዎች መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ስልጠና በመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬትና በeLearning ዳይሬክቶሬት በጋራ ቅንጅት መሰጠቱን ገልፀው ይህን አይነት የዲጂታል ሊትረሲ ስልጠናዎች እንደ ዩኒቨርሲቲ ተጠናክረው እንደሚሰጡ ዶ/ር ኡባህ አረጋግጠዋል፡፡ 

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መረጃና መገናኛ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር የሆኑት አቶ ስንታየሁ አለሙ በበኩላቸው እንዳሳወቁት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች Advisory Board ጋር በስልጠናው አሰጣጥ መርሃ ግብር በማውጣት በመጀመሪያ ዙር ከተማሪዎች የተውጣጡ በቁጥር አርባ (40) የሰልጣኝ አሰልጣኝ (Trainer of Trainee) በMicrosoft Office 365 Institutional email አጠቃቀምን ጨምሮ  e-SHE Success Suit Portal ላይ የዲጂታል ክህሎት ስልጠና መስጠት መቻሉን ገልጸው የToT ስልጠናውን የወሰዱ ተማሪዎች በ20 ኮምፒውተር ላብራቶሪ በማደራጀት በተከታታይ ሶስት ቀን የወሰደ ስልጠና የተሰጣቸው መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ይህን መሰል ስልጠናዎችን ለተማሪዎች የሚሰጥ መሆኑን ዳይሬክተሩ አቶ ስንታየሁ ተናግረዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው eLearning ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ተስፉ ጌትዬ በበኩላቸው በ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች  የተሰጠው የዲጂታል ክህሎት ስልጠና ቁጥራቸው  ከ1 ሺህ 8 መቶ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የተሰጠ መሆኑን ገልጸው ተማሪዎች በተዘጋጀው e-SHE Success Suit portal ላይ በመግባት የተዘጋጀላቸውን Free Course በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

Share This News

Comment