ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የሚጀምር ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማቋቋም የመጨረሻ የዝግጅት ምእራፍ ላይ መሆኑን አስታውቋል።
የሚቋቋመው ሞዴል ትምህረት ቤት ዩኒቨርሲቲው በዚሁ ጉዳይ ልይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የመከሩ ሲሆን ለትምህርት ቤቱ መቋቋም የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት "የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከማስተማርና ምርምር ጎን ለጎን የማኅበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቁመው አዲስ የሚከፈተው ሞዴል ትምህርት ቤት ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እየሰራ ያለውን ሰፊ ስራ የሚያሳይ ነው’’ ብለዋል።
የሚቋቋመው ሞዴል ትምህርት ቤት ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ከታች ጀምሮ ለማፍራት ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል ያሉት ዶ/ር ተማም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቀጣይነት ባለው መልኩ የሞዴል ትምህርት ቤቱን በማስፋፋት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሁም በትምህርት ጥራት ላይ ጉልህ ሚና የሚኖረው ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ/ም ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይ የተማሪዎች እና መምህራን ምልመላ መስፈርት፣ የመማሪያ ክፍሎች እና የትምህርት ግብዓቶችን የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።
Share This News