Logo
News Photo

የሐዘን መግለጫ

  • Event
  • February 13, 2026
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከዩኒቨርሲቲው ምስረታ ጀምሮ በመምህርነት እና በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ሲያገለግሉ የቆዩት መምህር ነጋ ገዛኸኝ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 5 ቀን 2018 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
መምህር ነጋ ግንቦት 9፣ 1968 ዓ/ም በጅግጅጋ ከተማ የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዛው ጅግጅጋ፣ በመምህርነት የዲፕሎማ ዲግሪ ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ፣ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡ መምህር ነጋ ገዛኸኝ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት 1999 ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ዩኒቨርሲቲውን በታማኝነት እና ቅንነት ያገለገሉ አንጋፋ የዩኒቨርሲቲው ምሁር ነበሩ፡፡ መምህር ነጋ በትዳር ከተጣመሩት ባለቤታቸው አንድ ሴት እና 3 ወንድ ልጆች አፍርተዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በመምህር ነጋ ገዛኸኝ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለመምህሩ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል፡፡

Share This News

Comment