የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1688 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመረቀ
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ መጋቢት 13 ቀን
2018 ዓ/ም በተለያዩ የትምህርት መስኮች እና በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን 1688 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ በድህረ ምረቃ 52፣ በቅድመ ምረቃ
1318 እንዲሁም በ
PGDT 318 ሲሆኑ በዛሬው እለት ከተመረቁት ተማሪዎች ውስጥ 430
ተመራቂዎች ሴቶች ናቸው፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት የተከበሩ አቶ አብዲ ሙክታር እንደተናገሩት ‘’ የዛሬ ምሩቃን ለሀገር እድገት እና ብልጽግና ለማረጋገጥ ስራን በመፍጠር፣ በታማኝነት እና ቅንነት ሀገርን በማገልገል የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል’’ ብለዋል፡፡ መንግስት የትምህርት ስብራቱን ለመጠገን ሰፊ የለውጥ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የጠቆሙት የተከበሩ አቶ አብዲ ‘’ትምህርትን በቴክኖሎጂ የማገዝ፣ የማዘመን እንዲሁም ኋላ ቀር አሰራሮችን በማሻሻል የትምህርት መስኩን ለመደገፍ መንግስት የጀመራቸው ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ጀምረዋል’’ ብለዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በበኩላቸው ‘’የደሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እንደ ሀገር የተቀረፁ የለውጥ አጀንዳዎችን ትኩረት በመስጠት እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው ዩኒቨርሲቲው በበጀት ዓመቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሞ የወሰዳቸውን ዋና ዋና ተግባራት በግማሽ ዓመቱ
87.7% ማሳካት ችሏል ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር፣ የትምህርት አሰጣጥ ሂደትን ከማዘመን፣ የመምህራንን አቅም ከማሻሻል፣ የትምህርት ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ፣ ችግር ፈቺ እና ጭብጥ ተኮር ምርምሮችን ከመስራት፣ የምሩቃን አቅምን የሚያሻሻሉ የስራ ቅጥር እና የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠናዎችን ከመስጠት አንጻር፣ የመሰረተ ልማትን ከማደስ፣ አዲስ የመገንባት እና የማሻሻል ስራዎችን ከመስራት አንጻር ተቋሙ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ገለጻ አድርገዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መሀል በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከተማራቸው 56 የትምህርት አይነቶች ውስጥ 50
A+ እንዲሁም A በማስመዝገብ አጠቃላይ ውጤት
4.00 ያስመዘገበው ተማሪ ዳዊት ከተማ የአመቱ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
Share This News